የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሕገ-መንግሥቱና በምርጫ ሕጉ መሠረት ከተሰጠው ሥልጣንና ኃላፊነት አንዱ የፖለቲካ ድርጅቶችን መመዝገብ፣ መከታተልና መቆጣጠር እንደሆነ ይታወቃል፡፡
በዚህም መሠረት የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቦ.ዴ.ፓ) ሊቀ-መንበር ታኅሣሥ 3 ቀን 2018 ዓ.ም. በቁጥር ቦሮ 2135 /2018 በተጻፈ ደብዳቤ የቦሮ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ጥር 22 ቀን 2012 ዓ.ም. ክልላዊ ፓርቲ ሆኖ እንዲንቀሳቀስ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠው የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ዕውቅና እንዲሠረዝ የፓርቲው ጠቅላላ ጉባዔ ኅዳር 15 ቀን 2018 ዓ.ም. ባካሄደው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ የወሠነ መሆኑን አሳውቆ፤ ቦርዱ በውሣኔው መሠረት ፓርቲውን ከምዝገባ እንዲሠርዝ በማለት አመልክቷል ።
በመሆኑ የፓርቲውን መሠረዝ አስመልክቶ ተቃውሞ ያለው ሰው ከነገ የካቲት 7 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በ14 ቀናት ውስጥ ተቃውሞውን ለቦርዱ ጽሕፈት ቤት እንዲያቀርብ ቦርዱ ያስታውቃል፡፡
ማስታወቂያ
የካቲት 6 ቀን 2018 ዓ.ም.