የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 7ተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ለማከናወን በርካታ የቅድመ ምርጫ ተግባራት እያከናወነ ይገኛል። በመሆኑም ቦርዱ ምርጫ የሚያስፈጽሙ ገለልተኛ የምርጫ ጣቢያ ሠራተኞችን በጊዜያዊነት ለመቅጠር ይፈልጋል።

በዚኽም መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መሥፈርቶች የምታሟሉ በሁሉም ክልሎች ላይ “በምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚነት” ማገልገል የምትፈልጉ አመልካቾች በሙሉ፤ ተከታዩን ማስፈንጠሪያ https://nebe-election.org/recruitment በመጠቀም ከታኅሣሥ 19 እስከ ታኅሣሥ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት እንድትመዘገቡ ቦርዱ ያሳውቃል። የምልመላ መሥፈርት፡-

  • ዕድሜው/ዋ ከ18 ዓመት በላይ የሆነ/ች፣
  • የማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነ/ች፣
  • የትምህርት ዝግጅት፦ 12ኛ እና ከዚያ በላይ የሆነ/ች፣
  • የሥራ ቦታ፦ ቦርዱ በሚያቋቁማቸው የምርጫ ጣቢያዎች፣
  • የክልሉን የስራ ቋንቋ መናገር እና መጻፍ የሚችሉ
  • የሥራ ቆይታ ፦ ለ2 ወር፣
  • ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ታኅሣሥ 19 ቀን 2018 ዓ.ም.

ማስታወቂያ
ታኅሣሥ 19, 2018