የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ “በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ ዐዋጅ ቁጥር 1133/2011” እና “በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ ቁጥር 1162/2011” መሠረት የፖለቲካ ፓርቲዎችን የመመዝገብ ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡
በዚኹ መሠረት እነአቶ ጌታቸው ረዳ ካሕሳይ “ዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት) ወይም Tigray Democratic Solidarity Party (Solidarity)“ በሚል ስያሜ ክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲ የምዝገባ ጥያቄ ያቀረቡ በመሆኑ፤ በዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 68 ንዑስ አንቀጽ 2 እና 3 መሠረት በፓርቲው ስም፣ ዐርማ ወይም ሌሎች ጉዳዮች ተቃውሞ ያለው ሰው፤ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከዛሬ ከጥቅምት 29 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በ14 ቀናት ውስጥ ተቃውሞውን ለቦርዱ ጽሕፈት ቤት እንዲያቀርብ ቦርዱ ያሳውቃል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ጥቅምት 29 ቀን 2018 ዓ.ም
ማስታወቂያ
ጥቅምት 29 ቀን 2018 ዓ.ም.