Skip to main content

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሥነ-ዜጋና የመራጮች ትምህርትን የተመለከተ የማኅበረሰብ ቲያትር በአዲስ አበባ ከተማ አቀረበ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሥነ-ዜጋና የመራጮች ትምህርትን የተመለከተ የማኅበረሰብ ቲያትር በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙት በኮከበ ጽባሕ እና በከፍተኛ 12 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች፤ እንዲሁም “በጃንሜዳ የስፖርትና የሥልጠና ማዕክል” እና በመዲናዋ ከፍተኛ የሕዝብ እንቅስቃሴ ከሚበዛባቸው አካባቢዎች አንዱ በሆነው በመገናኛ አካባቢ አቀረበ።

በከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ ውስጥ በቀረበው ቲያትር ላይ ከ9ኛ-12ኛ ክፍል የሚገኙ ተማሪዎች፣ መምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞች የተገኙ ሲሆን፤ በቲያትሩም ላይ ስለምርጫ ሥነ-ባህሪያት፣ ስለመሠረታዊ የዴሞክራሲ ጽንሰ-ሐሳብና መርኆዎች፣ ስለማኅበራዊ አካታችነትና አካል ጉዳተኝነት ዲሞክራሲ ለዜጎች የሚያስገኘውን መብት ተግባራዊ ከማድረግ ሊገድበን እንደማይገባ እያዝናና የሚያስተምር መልዕክት ተላልፎበታል።

ቦርዱ “ቪዥን አትዮጵያ ኮንግረስ ፎር ዴሞክራሲ” ከተባለው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ከተማ እያቀረበ ያለውን ትምህርታዊ ቲያትር በቀጣይም በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች የሚያቀርብ ይሆናል።

Share this post