የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሥነ-ዜጋና የመራጮች ትምህርትን የተመለከተ የማኅበረሰብ ቲያትር በባህርዳር ከተማ አቀረበ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ “አሣታፊ የማኅበረሰብ ቲያትር ለአካታች የሥነ-ዜጋና የመራጮች ትምህርት” በሚል ርዕስ በባህር ዳር ከተማ በሚገኘው ፓፒረስ አደባባይ (ሰንበት ገበያ) ላይ ቲያትር አቀረበ። በኪነ-ጥበብ ሥራው ላይ ሥርዓተ ፆታና ማኅበራዊ አካታችነትን፣ ሐሰተኛ መረጃን መከላከልና ኃቅን ማጣራትን፣ የዜጎች መብቶችና ግዴታዎችን፣ ሰላማዊ የግጭት አፈታትን፣ የእያንዳንዱ ዜጋ የምርጫ ተሣትፎና የድምፅ ዋጋን የተመለከቱ የግንዛቤ ማስጨበጫ መልዕክቶች ተላልፈውበታል።
ቦርዱ ከአማራ ክልል “ፎቶ’ግራፈር እና ቪዲዮ’ግራፈር ባለሙያዎች ማኅበር” ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ሕዝብን እያዝናኑ ግንዛቤ የማስጨበጫ የኪነ-ጥበብ ሥራ በቀጣይ በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች የሚካሄድ ይሆናል።













