የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የማኅበረሰብ ቲያትር በመቐለ ከተማ አካሄደ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመቐለ ከተማ በሚገኙት መቐለ ዩኒቨርስቲ ዓዲሓቂ ካምፓስ እና በደሳለኝ ሆቴል ለተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የማኅበረሰብ ቲያትር አቀረበ። የኪነ-ጥበብ ሥራው ከተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች ለተውጣጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች አንዲሁም በትግራይ ክልል ለሚንቀሳቀሱ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የቀረበ ሲሆን፤ በተመሳሳይ መልኩ በመቐለ ዩኒቨርስቲ አዲ ሀቂ ካምፓስ ለሚገኙ ተማሪዎችም ቀርቧል።
ቦርዱ ፍኖት የሕግ ባለሙያዎች ማኅበር ከተባለ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ቲያትር ዋና ዐላማ፤ሰላም ምርጫን ጨምሮ ለሁሉም ነገር መሠረት እንደሆነና እያንዳንዱ ዜጋ ሰላምን ለማስፈን ኃላፊነት እንዳለበት ግንዛቤ መፍጠር ሲሆን፤ በቀጣይም ፍኖት የሕግ ባለሙያዎች ማኅበር በትግራይ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ለሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች የኪነ-ጥበብ ሥራውን ለማቅረብ ዝግጅቱን አጠናቋል።



