የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት የተሳትፎ ጥሪ ማስታውቂያ
በስነዜጋ እና በዲሞክራሲያዊ ምርጫ እሳቤዎች ዙርያ የኪነጥበብ ሥራዎችን ለማዘጋጀት ፍላጎት ላላቸው ተቋማት የቀረበ ጥሪ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለዜጎች በስነዜጋ እና በዲሞክራሲያዊ ምርጫ እሳቤዎች ዙርያ አካታች እና ተደራሽ የሆኑ የኪነጥበብ ሥራዎችን በተለይም የማህበረሰብ አቀፍ ቲአትር እና ሙዚቃ ነክ የኪነጥበብ ሥራዎችን ለማዘጋጀት ፍላጎት ላላቸው የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት ጥሪ ያቀርባል። በመሆኑም በዚሁ ጉዳይ ላይ ፍላጎት እና ልምዱ ያላችሁ መንግስታዊ ያልሆናችሁ ተቋማት በተናጠል ወይም በጋራ በስነዜጋ እና በዲሞክራሲያዊ ምርጫ እሳቤዎች ዙርያ የኪነጥበብ ሥራዎችን ለማቅረብ ዝርዝር የፍላጎት መግለጫ ወረቀት (Expression of interest) እንዲሁም የመተዳደሪያ ደንብ ቅጂ ለቦርዱ እንድታቀርቡ ጥሪ ያቀርባል።
ማንኛውም የኪነጥበብ ሥራዎችን ለማዘጋጀት እና ለህዝብ በነጻ ለማቅረብ የሚያስብ የሲቪል ማህበረሰብ ተቋም የሚመለከቱትን ዋና ዋና ተግባራትን ያሟላ የፍላጎት መግለጫ ሊያቀርብ ይገባል።
- ተቋሙ ሊያከናውነው ያቀደው የኪነጥበብ ሥራ ግልጽ ዓላማ፤
- የኪነጥበብ ሥራው የትኩረት አቅጣጫ፣ ይዘት እና የሚተላለፉ ዋና ዋና መልእክቶች
- ተቋሙ ሊያከናውነው ያቀደውን ሥራ የሚከናወንበት እና የሚቀርብት መንገድ (mode of engagement and delivery)
- የኪነጥበብ ሥራው የሚቀርብበት ቦታ
- ተቋሙ ያዘጋጀው የኪነጥበብ ሥራ የስነምግባር ደንብ (code of conduct፤
- የኪነጥበብ ሥራው ብዛት፣ የተሳታፊዎች ቁጥር እና ሁኔታ፤
- የኪነጥበብ ሥራው የሀገራችንን ብዝሀነት ያማከል መሆን ይኖርበታል
- የኪነጥበብ ሥራው መልእክት ሊያስተላልፍላቸው የሚፈልገው የህብረተስብ ክፍሎች (Target Audience)፤
- የኪነጥበብ ሥራው ለህዝብ የሚቀርብበት ሁኔታ እና የተደራሽነት መጠን፤
- ሥራውን ለማከናወን ተቋሙ ያዘጋጀው በጀት ፤
- የሚተላለፈው መልእክት ተጋላጭ የህብረተሰብ ከፍሎችን (ሴቶች፣የአካል ጉዳተኞች ፣ተፈናቃዮች)ያማከለ መሆኑ፤
- ተቋሙ ሥራውን ለማከናወን የሚያወጣው ገንዘብ ምንጭ፤
- ተቋሙ የኪነጥበብ ሥራውን የሚያከናውንባቸው ቋንቋዎች እና የመሳሰሉት ናቸው።
ከላይ ከተጠቀሱት ዋና ዋና ጉዳዮች በተጨማሪ ምክረሃሳብ የሚያስገቡ ተቋማት አስፈላጊ ነው የሚሉትን ዝርዝር ዕቅድ በምክረሃሳባቸው ውስጥ አካተው ማቅረብ ይችላሉ። የፍላጎት መግለጫው ከህዳር 9 እስከ ህዳር 16 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ በቦርዱ ዋና መስሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 106 በግንባር ወይም በ votersedu [at] nebe.org.et ኢሜይል አድራሻ ሊቀርብ ይችላል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
አዲስ አበባ
ሕዳር 7 ቀን 2017 ዓ.ም.