የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛው አጠቃላይ ምርጫን ለማስፈጸም 140 ሺህ በላይ አስፈጻሚ ለመሆን የሚችሉ ሰዎቸን ምልመላ የሚያከናውንበት ሂደት በማጠናቀቅ የአስፈጻሚዎችን ፍቃደኝነትን፣ ገለልተኝነትን እና ብቃትን በማረጋገጥ ስራ ላይ አንደሆነ ይታወቃል።

ምርጫ አስፈጻሚዎች የምርጫ ሂደቱ ዋና አካል መሆናቸውን በመረዳት እና ስራውም ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚጠይቅ በመሆኑ እንዲሁም የምርጫ ሂደቱ ከተጀመረ በኋላ የሰው ሃይል እጥረት እነዳይፈጠር በማሰብ ተጨማሪ የሰው ሃይል ምልመላ ማከናወን እንዳለበት አምኗል።

በዚህም መሰረት

- ለምርጫ አስፈጻሚነት በገለልተኝነት አገራችሁን ለማገልገል የምትፈልጉ

- ምንም አይነት ፓርቲ አባልነት፣ የዝቅተኛ የአስተዳደር እርከኖች ላይ ሰርታችሁ የማታውቁ

- ከሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ውጪ በሌሎች የቀድሞ ምርጫ የማስፈጻም ተግባራት ላይ ተሳትፋችሁ የማታውቁ

- የመጀመሪያ ዲግሪ ወይም ተመጣጣኝ ረጅም አመት የስራ ልምድ ያላችሁ

የሚከተለውን ፎርም በመጠቀም በሚቀጥሉት አራት ቀናት እስከ የካቲት 27 ድረስ ብቻ ማመልከት ትችላላችሁ።

የስራው ቆይታ ለ4 ወራት ሲሆን፣ የቀን አበል፣ አስፈላጊ የሆኑ ቦታዎች/ ሁኔታዎች ላይ ጥበቃ፣ እንዲሁም ስራውን ለማከናወን የሚያስፈልጉ ማንኛውንም ነገሮች ቦርዱ ያሟላል።

የስራ ልምድ ሰርተፍኬት፣ የድጋፍ ደብዳቤ በቦርዱ የሚሰጥ ይሆናል።

https://nebe.org.et/pworkers/

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

የካቲት 24 ቀን 2013 ዓ.ም 

የስራ ማስታወቂያ
የካቲት 24 ቀን 2013 ዓ.ም