የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በህገ መንግሥቱ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ በአጠቃላይ አምስት (5) ሀገር አቀፍ ጠቅላላ ምርጫዎች፣ ስድስት (6) ህዝበ ውሳኔዎች እና ሌሎች የማሟያ እና የአካባቢ ምርጫዎችን በአጠቃላይ አስራ አራት (14) ምርጫዎችን አስፈጽሟል፡፡ እስካሁን በተከናወኑት አምስት ሀገር አቀፍ ጠቅላላ ምርጫዎች ለአምስት መቶ አርባ ሰባት (547) የፌዴራል መቀመጫዎች እና ለስድስት መቶ ሃምሳ አራት (654) የክልል መቀመጫዎች እጩዎች ቀርበዋል፡፡ የሀገር አቀፍ ጠቅላላ ምርጫዎች የተጠቃለለ መረጃ ከስር ይገኛል፡፡