በዲሞክራሲያዊ አስተዳደር ሥርዓት ዜጎች ነጻ የሆነ ሀሳባቸው የሚገልጹበት እና ሀገርን የሚያስተዳደሩ ብቁ ዕጩዎችን ለሥልጣን የሚያበቁበት አንዱ መንገድ ድምፅ መስጠት ወይም መምረጥ ነው፡፡
ስለዚህም የዜጎች መምረጥ

  • የዲሞክራሲያዊ አስተዳደር ቁልፍ ጽንሰ ሃሳብ የሚረጋገጥበት፣
  • በህዝብ የተወከለ መንግሥትን የሚያቋቁሙበት፣
  • እኩልነትን የሚያረጋግጡበት፣
  • የሀገር ፍቅርን የሚገልጹበት እና ዘመናዊነትን የሚለማመዱበት፣
  • በሀገራቸው ጉዳይ ላይ የየግል አሻራቸውን የሚያኖሩበት፣
  • የመረጧቸው ተወካዮችን ተጠያቂነትን የሚያረጋግጡበት፣
  • በተለያዩ ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ መድረኮች የሚወክላቸውን አስተዳደራዊ አካል የሚመርጡበት፣
  • መንግሥት ለዜጎቹ የሚጠቅም ፓሊሲዎች እንዲያዘጋጅና እንዲተገብር የሚያደርጉበት፣
  • ሃሳብን የመግለጽ እድልን የሚያረጋግጡበት፣
  • የመልካም አስተዳደር መስፈንን የሚከታተሉበት ዓይነተኛ መሳሪያ ነው፡፡ በተጨማሪም ዜጎች አለመምረጥ የሚያስከትለውን አሉታዊ ተጽዕኖዎች ማለትም፣  
  • ሊወክላቸው በማይችል ወኪል መተዳደር፣
  • ባልመረጧቸው እና ባልደገፏቸው የአስተዳደር አካላት ውሳኔ እንዲሁም አስተዳደራዊ ሥርዓት ስር ተገዢ መሆን፣
  • ዜጎች የደገፏቸው የተሻለ የአመራር ሥርዓት ያለው ተወዳዳሪ ተመራጭ አለመሆን፣

በተጨማሪም ዜጎች አለመምረጥ የሚያስከትለውን አሉታዊ ተጽዕኖዎች ለመከላከል ዜጎች የዜግነት መብታቸውን በመጠቀም ድምፅ መስጠት ይኖርባቸዋል፡፡