የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዋና መስሪያ ቤት ደረጃ የጀመረውን ውስጣዊ አደረጃጀት ሪፎርም በክልል ደረጃ በማስፋት በክልሎች የሚገኙት ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶቹን እንደአዲስ እያደራጀ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ ከነዚህም መካከል

-የአማራ ክልል የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት ኃላፊ
-የሀረሪ ክልል የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት ኃላፊ
-የቤኒሻንጉል ክልል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት ኃላፊ
-የድሬዳዋ ከተማ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት ኃላፊ
ለመመልመል ባወጣው ተደጋጋሚ ማስታወቂያ በቂ ቁጥር ያለው ተወዳዳሪ ሊገኝ ባለመቻሉ የሚከተሉትን መስፈርት የሚያሟሉ አመልካቾች እስከ ታህሳስ 15 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ማመልከት የሚችሉ መሆኑን ያሳውቃል፡፡

በዚህም መሰረት በክልል የምርጫ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊነት በዕጩነት የሚቀርቡ አመልካቾች ማሟላት የሚኖርባቸው መስፈርቶች፡-
1.ኢትዮጵያዊ ዜጋ የሆነ/የሆነች፣
2.መደበኛ አድራሻው በምርጫ ክልል ውስጥ ሆኖ የፌዴራሉን መንግስት፣ የሚወዳደርበትን ክልል የሥራ ቋንቋ የመናገርና የመፃፍ ክህሎት ያለው/ያላት፤
3.በአካባቢው ነዋሪ ሕዝብ አመኔታ ያተረፈ/ያተረፈች እና መልካም ሥነ ምግባር ያለው/ያላት፤
4.የማንኛውም ፖለቲካ ድርጅት አባል ያልሆነ/ያልሆነች
5.በትምህርት ዝግጅት በተለይ በሕግ፣ በፖለቲካ ሳይንስ፣ በህዝብ አስተዳደር፣ በስታቲስቲክስ፣ በማኔጅመንት፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂና ከምርጫ ጉዳዮች ጋር ተዛማጅነት ባላቸው የትምህርት ዘርፎች ቢያንስ በአንዱ የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው/ያላት፤
6.አመልካች የማስተርስ ዲግሪ ያላት/ያለው ከሆነ የአራት ዓመት የሥራ ልምድ፤ የመጀመሪያ ዲግሪ ያላት/ያለው ከሆነ ደግሞ የአምስት ዓመት የሥራ ልምድ
7.የምርጫ ህጉን፣ ደንብና መመሪያዎችን አንብቦ/አንብባ በመረዳት መተግበር የምትችል/የሚችል
8.በተቋም ነጻነትና እና በገለልተኛነት መርህ መሰረት ለማገልገል ዝግጁ እና ሙሉ ፍቃደኛ የሆነች/የሆነ
አመልካች እጩዎች ለስራው ያላቸውን መነሳሳት የሚገልጽ አንድ ገጽ ማመልከቻ፣ የተሟላ ካሪኩለም ቪቴ፣ የትምህርት ማስረጃ እንዲሁም ሁለት ስለአመልካቹ ብቃት የሚገልጹ ለአመልካቹ ቅርብ ከሆኑ ሰዎች የተጻፉ የድጋፍ ደብዳቤዎችን እስከ ታህሳስ 15 ቀን 2012 ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
የተሟላ ማመልከቻቸውን በኢሜል- electionsethiopia [at] gmail.com፣ በአካል ፍላሚንጎ አካባቢ የሚገኘው የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ዋና መስሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 503 በመቅረብ፤ በፈጣን መልዕክት /EMS/ ወይም በፖስታ ሳጥን ቁጥር 40812 መላክ ይችላሉ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

የስራ ማስታወቂያ
ታኅሣሥ 9 ቀን 2012 ዓ.ም.