Skip to main content

ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ6ኛው ዙር የጠቅላላ እና የድጋሚ ምርጫ ባልተካሄደባቸው የቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ አፋር፣ ሶማሌ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ሰኔ 9 ቀን 2016 ዓ.ም. የሚካሄደውን ምርጫ መዘገብ ለምትፈልጉ የመገናኛ ብዙኃን የቀረበ ጥሪ

የመገናኛ ብዙኃን ቀጣዩ የ6ኛው ዙር የጠቅላላ እና የድጋሚ ምርጫ ባልተካሄደባቸው የቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ አፋር፣ ሶማሌ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ምርጫው ፍትሐዊ፣ ገለልተኛና ተዓማኒ እንዲሆን የሚያበረክቱት ሚና ከፍተኛ መሆኑን በመገንዘብ፤ የመገናኛ ብዙኃኑና ጋዜጠኞች በምርጫ ጣቢያዎች ተገኝተው ለመዘገብ የሚያስችል የፍቃድ ጥያቄያቸውን ለቦርዱ እንዲያቀርቡ ይህንን ጥሪ ማድረግ አስፈልጓል፡፡ በዚህ መሠረት ለመዘገብ ጥያቄ የሚያቀርቡ የመገናኛ ብዙኃን፡

  • ቦርዱ ያዘጋጀውን የማመልከቻ ፎርም
  • የጋዜጠኞች ዝርዝር የሚገልጽ ፎርም
  • የሚዲያ ተቋሙ የሚያሠማራቸው ጋዜጠኞች የገለልተኝነት ማረጋገጫ ቃለ-መኃላን ጨምሮ የተለያዩ አስፈላጊ ተያያዥ ሠነዶችን በማቅረብ የዘገባ ዕውቅና እንዲሰጣቸው ማቅረብ ይችላሉ።

መገናኛ ብዙኃን የማመልከቻ ቅጹንና አስፈላጊ ሠነዶችን ከቦርዱ ድረ-ገጽ ወይም ቦሌ መንገድ ፊላሚንጎ ሬስቶራንት ፊት ለፊት ከሚገኘው የቦርዱ ዋና መሥሪያ ቤት መውሰድ የምትችሉ ሲሆን፤ የተጠናቀቁ ማመልከቻዎቻችሁን በኢ-ሜል አድራሻችን media [at] nebe.org.et መላክ ወይም ለዋናው መሥሪያ ቤት እና ለክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከግንቦት 02 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ማስገባት ትችላላችሁ።

የማመልከቻ ቅጹንና አስፈላጊ የሆኑ ሠነዶችን ዝርዝር ከሥር በሚገኘው ሊንክ አማካኝነት ማግኘት ይችላሉ።

  1. የመገናኛ ብዙሃን እና የጋዜጠኞች የምርጫ አዘጋገብ የስነ ምግባር እና አሰራር መመሪያ ቁጥር 02/2013
  2. ምርጫውን ለመዘገብ ጥያቄ ለሚያቀርቡ የመገናኛ ብዙሃኃ የማመልከቻ ቅጽ
  3. ዕውቅና እንዲሰጣቸው የተጠየቁ ጋዜጠኞች ስም ዝርዝር
  4. የምርጫውን ሂደት ለመዘገብ ፈቃድ እንዲሰጠው በጠየቀ የሚዲያ ተቋም የበላይ ኃላፊ የሚሞላ ቃለ-መኃላ

ከዚህ ማመልከቻ ቅጽ ጋር ተያይዘው መቅረብ ያለባቸው ሠነዶች ዝርዝር (ለማረጋገጫ የሚጠቅም)

  • የመገናኛ ብዙሃኑ የብሮድካስት ፈቃድ
  • ምርጫውን ለመዘገብ የተመደበው ጋዜጠኛ መታወቂያ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

Share this post