Skip to main content

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ታኅሣሥ 21 ቀን 2015 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ ለአርጎባ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት /አ. ህ. ዴ. ድ/ ነሐሴ 23 ቀን 2014 ዓ.ም. ያካሄደውን ጠቅላላ ጉባዔ በሚመለከት ቦርዱ ያሳለፈዉ ዉሳኔ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ታኅሣሥ 21 ቀን 2015 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ የአርጎባ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት /አ. ህ. ዴ. ድ/ ነሐሴ 23 ቀን 2014 ዓ.ም. ያካሄደውን ጠቅላላ ጉባዔ በሚመለከት ፓርቲው ከሪፖርት ጋር አያይዞ ያቀረባቸውን ሠነዶች ከሕጉ፣ ከፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ እና የቦርዱ ታዛቢዎች ካቀረቡት ሪፖርት አንጻር መርምሮ ውሣኔ አሣልፏል።

ቦርዱ ባደረገው ምርመራ ፓርቲው ያካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ ያሻሻለው የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ ላይ ያሉ ከዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 ጋር የሚቃረኑ አንቀጾች ተፈጻሚ እንዳይሆኑ፤ እንዲሁም ጠቅላላ ጉባዔው በቀጣይ ስብሰባው አስፈላጊውን ማስተካከያ አድርጎ ሪፖርት እንዲያቀርብ የወሠነ ሲሆን፤ ፓርቲው ነሐሴ 23 ቀን 2014 ዓ.ም. ያካሄደውን ጠቅላላ ጉባዔ እና የተላለፉ ውሣኔዎችን የመዘገበ መሆኑን ቦርዱ ለፓርቲው በላከው ደብዳቤ አሳውቋል።

የውሣኔውን ሙሉ ዝርዝር ደብዳቤ እዚህ ላይ ያገኙታል

Share this post