በዛሬው እለት በሐረሪ፣ በሶማሌ እና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ክልል ድምጽ አሰጣጥ እና ህዝበውሳኔ ሲከናወን ውሏል። ነገር ግን ተጨማሪ የድምጽ መስጫ ሰአት የሚያስፈልጋቸው ምርጫ ክልሎች በመገኘታቸው እና ድምጻቸውን መስጠት የሚፈልጉ ዜጎች እድሉን እንዳያጡ በማሰብ በአዋጅ 1162/ 2011 አንቀፅ 49 (4) መሰረት በሚከተሉት ቦታዎች የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ እስከ ምሽቱ 2 ሰአት ድረስ መራዘሙን ቦርዱ ያሳውቃል።

1. በሐረሪ ክልል በሚገኙ ሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች

2. ከሐረሪ ክልል ውጪ ለሐረሪ ክልል የሚመርጡ ምርጫ ጣቢያዎች

3. ሕዝበውሳኔ በሚካሄድባቸው ሁሉም የምርጫ ክልሎች (ህዝበውሳኔን ለብቻ ለሚያካሂዱ እንዲሁም ህዝበውሳኔን እና ምርጫን ለሚያካሂዱ በሙሉ)

አስፈጻሚዎች ከላይ ከተጠቀሱት ቦታዎች ውጪ ባሉ ቦታዎች 12 ሰአት ሲሞላ ሰልፍ ላይ ያሉ መራጮችን በማስተናገድ ምርጫውን እንዲያጠናቅቁ እንዲሁም 12 ሰአት ላይ መራጮችን አስተናግደው ያጠናቀቁ ጣቢያዎች በህጉ መሰረት ታዛቢዎች በተገኙበት ቆጠራን እንዲጀምሩ ቦርዱ ያሳስባል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም