6ተኛው አገር አቀፍ ምርጫ በትላንትናው እለት በሰላም እንደተጠናቀቀ ይታወሳል። በዚህም መሰረት በዛሬው እለት ምርጫ ጣቢያዎቹ ላይ የተጠናቀቁ የድምፅ ቆጠራ ውጤቶች ይፋ እየሆኑ ይገኛል። በትላንትናው እለት የድምጽ አሰጣጥ ሂደት ሳይጠናቀቅ በቀረባቸው ቦታዎችም በተመሳሳይ የድምፅ መስጠት ሂደት ዛሬ የሚከናወን ይሆናል።

በዚህም መሰረት

  1. በሲዳማ ክልል በሁሉም ምርጫ ክልሎች ከጠዋቱ 5 ሰአት ጀምሮ የድምጽ አሰጣጡ ሂደት የቀጠለ ሲሆን በዛሬው እለት ይጠናቀቃል።
  2. በጋምቤላ ክልል ባሉ የተወሰኑ የምርጫ ክልሎች ተቋርጦ የነበረው የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ዛሬ ከቀኑ 8 ሰአት ጀምሮ የሚቀጥል ሲሆን በዛሬው እለት ይጠናቀቃል።
  3. በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሁለት ምርጫ ክልሎች ያለው ድምጽ አሰጣጥ ሂደት ለጊዜው የቆመ ሲሆን ቁሳቁሶች በሙሉ ታሽገው እንዲጠበቁ ቦርዱ ለአስፈጻሚዎች ያሳውቃል።

በዚህም መሰረት ቦርዱ የሚቀጥለው የድምፅ አሰጣጥ ሁኔታ እና እስካሁን ያለውን ሂደት ገምግሞ ውሳኔ ላይ ደርሶ የሚያሳውቅ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ሰኔ 15 ቀን 2013 ዓ.ም