Skip to main content

ለአካል ጉዳተኞች አጋዥ የምርጫ ቁሳቁሶች እና ትምህርት መሰጠት ተጀመረ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዐዋጅ እንደገና ከተቋቋመበት ጊዜ አንሥቶ በትኩረት እየሠራባቸው ካላቸው ተግባራት አንዱ የአካል ጉዳተኛና የሥርዓተ-ፆታ አካታችነት ተጠቃሽ ናቸው። ይህንንም ይረዳ ዘንድ የምርጫ ሕጉን ማዕቀፎች በዐይነ-ሥውራን ዘንድ ተዳራሽነቱን ለማስፋት ይረዳ ዘንድ ያሳተማቸውን ብሬሎች በአካል ጉዳተኞች የመራጮች ትምህርትና በመታዛቢነት ለተሠማሩ ለሲቪል ማኅበራት መስጠት ጀመረ።

ቦርዱ ብሬሎችን ከመስጠት በተጨማሪ በታዛቢነት ለተሠማሩ ሲቪል ማኅበራት ምርጫ ጣቢያዎች ውስጥ ለሚኖራቸው ሕጋዊ እንቅስቃሴ ዕውቅና የሚያስገኝላቸውን ባጅ መስጠት ጀምሯል።

Share this post