የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቀጣዩን 6ተኛ አገራዊ ምርጫ ለማካሄድ የተለያዩ መመሪያዎችን በማጽደቅ ላይ እንደሆነ ይታወሳል፡፡ ከነዚህም መመሪያዎች መካከል አንዱ በምርጫ ሂደት ወቅት የኮቪድ 19 ስርጭትን መከላከል እና መቆጣጠር የሚያስችል መመሪያ ነው፡፡ የዚህ መመሪያ ዋና ዓላማ በምርጫ ሂደት ወቅት የኮቪድ 19 ስርጭትን መከላከል እና መቆጣጠር በቅድመ ምርጫ፣ በድምጽ መስጫ ቀን እና በድህረ-ምርጫ ወቅት ከምርጫ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ተግባራት ሁሉ የኮቪድ 19 ስርጭትን እንዳይጨምሩ ማድረግ ነው፡፡ ለቦርዱ እና በምርጫ ባለድርሻ አካላት እንዲሁም የምርጫ አስፈፃሚ አካላት በሙሉ ሊሟሉላቸው የሚገቡ ሁሉም የኮቪድ 19 አስፈላጊ መስፈርቶች የዚህ ረቂቅ መመሪያ የትኩረት አቅጣጫዎች ናቸው፡፡

ይኽንን ረቂቅ መመሪያ ከሕዝብ በሚሰበሰቡ ገንቢ ሀሳቦች ለማዳበር ይረዳ ዘንድ ለአንድ ሳምንት ለሚቆይ ጊዜ ክፍት አድርጓል። ስለሆነም ዛሬ ታኅሣሥ 26 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ሳምንት ለሚቆይ ጊዜ ያላችሁን ሀሳብና አስተያየት በሚከተለው የኢሜል አድራሻ legal [at] nebe.org እንዲሁም በገፃችን መልዕክት ማስቀመጫ አማካኝነት ለቦርዱ የሕግ ክፍል እንድትልኩ ስንል በአክብሮት አንጋብዛለን።

ረቂቅ መመሪያውን ለማግኘት ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ:- ምርጫ ሂደት ወቅት የኮቪድ 19 ስርጭትን መከላከል እና መቆጣጠር የሚያስችል ረቂቅ  መመሪያ

የጥሪ ማስታወቂያ
ታኅሣሥ 26 ቀን 2013 ዓ.ም