የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቦርድ አመራር አባል እና ሰራተኞች የጋና ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ሂደትን ተከታተሉ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቦርድ አመራር ፍቅሬ ገብረህይወት የተመራው የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰራተኞች ቡድን የጋራ ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ሂደትን፣ የድምጽ መስጫ ቀን የተደረጉ ተግባራትን፣ የኮቪድ ወረርሽን በመከላከል የተከናወነውን የድምጽ መስጠት ሂደት ተከታትለዋል፡፡
በአራት ቀናት ቆይታቸውም ምርጫን የኮቪድ ወረርሽኝ ጥንቃቄ በማድረግ ለማከናወን የተደረጉ ተግባራትን፣ የምርጫ አስፈጻሚው ተቋምን አሰራር፣ የምርጫ ክልል ደረጃ ውጤት ቆጠራ፣ ድመራ እና ይፋ ማድረግን የተከታተሉ ሲሆን ከጋና ምርጫ ኮሚሽን አመራር አካላትም ጋር ተነጋግረዋል፡፡ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ልኡካን ምርጫውን ከመታዘብም በተጨማሪ በተለይ በኮቪድ ወረርሽኝ ስጋት ውስጥ ሆኖ ምርጫ ማከናወን የሚያስፈልጉትን የበጀት እና የሎጄስቲክስ ዝግጅቶችን ከጋና ምርጫ ልምድ መቅሰም ችለዋል፡፡
የጋራ ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ሰኞ ህዳር 28 ቀን 2013 መካሄዱ ይታወሳል፡፡