Skip to main content

የምርጫ ቦርድ አዲሱ የምርጫ ህግ፣ መመሪያዎች፣ ህጋዊ ማዕቀፍ ነክ ጉዳዮች ለውይይት ቀርበዋል

የካቲት 6 ቀን 2012 ዓ.ም.    

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአዲስ መልክ እያከናወነ ያለውን ተቋማዊ ግልጽነትን እና ተአማኒነትን የሚያሳዩ እንዲሁም የተቋም ማንነት ለውጥን የሚወክሉ መገለጫዎችን በማካተት የተቋሙን አዲስ አርማ አዘጋጅቷል። ይህም አርማ የተዘጋጀው የቦርዱን ግልጽነት በሚያሳይ እና አንድ ወጥ የሆነ የተቋም ማንነት ምስል በሚፈጥር መልኩ ነው። የዛሬው ስብሰባ አንዱ ዓላማም ይህንኑ የቦርዱን አዲስ አርማ ለባለድርሻ አካላት እንዲሁም ለሕዝብ ማስተዋወቅ ነው።

በሁለተኛው ፓነል ለውይይት የቀረቡ ነጥቦች፦
- ህጋዊ ማዕቀፍ ነክ ጉዳዮች፣
- አዲሱ የምርጫ ህግ፣ መመሪያዎች፣ የምክክር ሂደቶች እንዲሁም የምርጫ ደህንነትና ጸጥታ በምርጫ ወቅትና ከምርጫ ጋር የተያያዙ ግጭቶች አፈታት፣
በጌታሁን ካሳ (ዶ/ር) - የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አመራር አባል
- የፓለቲካ ፓርቲ ጉዳዮች፣ የፓለቲካ ፓርቲ አዋጅ 1162 ሟሟላት ሂደት እና በቦርዱ በኩል የተሠሩ ሥራዎች፣
- ከፓለቲካ ፓርቲዎች ጋር የሚደረጉ ምክክሮች፣ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች እና ምላሽ በውብሸት አየለ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ እና ናትናኤል መላኩ (የፓለቲካ ፓርቲዎች ባለሞያ)፣
በዚሁ ዕለት የመጪው ምርጫ የሚካሄደው ነሐሴ 23 ቀን 2012 ዓ.ም. መሆኑን ዛሬ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ አድርጓል።

ሙሉ ፕሮግራሙን  ዩትዩብ ገፃችን ላይ ያገኙታል

YouTube: National Election Board of Ethiopia - NEBE ምርጫ ቦርድ 

 

Share this post