በቅርቡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የእውቅና ሰርተፍኬትና ጊዜያዊ የምዝገባ ፈቃድ የሰጣቸው ፓርቲዎች
ጥር 13 ቀን 2012 ዓ.ም.
በቅርቡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የእውቅና ሰርተፍኬትና ጊዜያዊ የምዝገባ ፈቃድ የሰጣቸው ፓርቲዎች የሚከተሉት ናቸው፦
1. ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ፣
2. አንድ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣
3. አማራ ጊዮናዊ ንቅናቄ፣
4. እናት ፓርቲ፣
አገው ብሔራዊ ሸንጎ እና ብልጽግና ፓርቲም የሙሉ እውቅና ምዝገባ ፈቃድ ማግኘታቸው ይታወሳል። ጊዜያዊ የምዝገባ ሰርተፍኬት ምንድነው?
ጊዜያዊ የምዝገባ ሰርተፍኬት በአዋጅ 1162 አንቀጽ 66 ንኡስ አንቀጽ 3 - 5 ድረስ ባለው የህግ አግባብ መሠረት የሚሰጥ ሲሆን ጊዜያዊ ሰርተፍኬተ ለማግኘት፦
- ማመልከቻ፣
- በጽሁፍ የሚቀርብ የምዝገባ ጥያቄ፣
- ለአገር አቀፍ ቢያንስ 200፣ ለክልላዊ ፓርቲ ቢያንስ 100 አመልካቾች የፈረሙበት የስብሰባ ቃለ ጉባኤ፣
- የሚመሠረተው የፓለቲካ ፓርቲ ጊዜያዊ ስም፣
- የምርጫ ህጉንና ተያያዥ ህጎችን የሚያከብሩ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ እና ቦርዱ የሚወስነውን የአገልግሎት ክፍያ ፍቃዱ የሚያገለግለው፣
- ለሦስት ወራት ብቻ (አመልካቾች በቂ ምክንያት አቅርበው የጠየቁ እንደሆነ ለተጨማሪ 3 ወር ሊራዘም ይችላል)።