ስለ ዲጂታል መራጮች ምዝገባ የተሰጠ ማብራሪያ
የመጪውን ምርጫ ግልጽ፣ ተዓማኒ እና ቀልጣፋ ለማድረግ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማሳደግ አንዱ የሪፎርም አካል መሆኑ ይታወቃል።
በዚህም መሠረት የዲጂታል መራጮች ምዝገባ ሥርዓትን በሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅቶች ተጠናቀው ወደ ተግባር ተገብቷል። ይሁን እንጂ፣ በዛሬው ዕለት የተጀመረው የዲጂታል መራጮች ምዝገባ በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ሳይሆን በተመረጡ ጣቢያዎች ላይ ብቻ የሚከናወን መሆኑን በድጋሚ ለሕዝብ ግልጽ ማድረግ እንወዳለን።
መራጮች ሊገነዘቧቸው የሚገቡ ዋና ዋና ነጥቦች፦
የዲጂታል ምዝገባው የሚካሄደው አስቀድመው ለዚህ ተግባር በተለዩ ውስን ጣቢያዎች ብቻ ነው።
በዲጂታል ምዝገባ በማይካሄድባቸው ሌሎች ጣቢያዎች ሁሉ፣ የመራጮች ምዝገባ እንደተለመደው በመዝገብ (በማኑዋል) የሚቀጥል ይሆናል።
መራጩ ሕዝብ መረጃዎችን ከቦርዱ ይፋዊ የመረጃ ምንጮች ብቻ በመከታተል፣ ለምዝገባ ሂደቱ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
ጠቃሚ መረጃዎች
የዲጂታል መራጮች ምዝገባ የሚከናወንባቸውን የምርጫ ጣቢያዎች ዝርዝር ይህንን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ፡።
ለተጨማሪ መረጃ፦ በነፃ የስልክ መስመር 📞7555 ይደውሉ
