የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የፃፈዉ ደብዳቤ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም. ከጠቅላላ ጉባዔ፣ ከኦዲትና በሴት አባላት ቁጥር አማካኝነት ከሚገኝ የገንዘብ ድጋፍ ጋር በተገናኘ 11 ፓርቲዎች ላይ የዕግድ ውሣኔ ማሳለፉ ይታወቃል። ቦርዱ ከታገዱት ፓርቲዎች ውስጥ የይቅርታና የመከላከያ መልስ ያቀረቡትን አምስት ፓርቲዎች ጉዳይ መርምሮ፤ ፓርቲዎቹ ያለፈውን ስህተት እንደማይደግሙና በቀጣይም በሚያቀርቧቸው መረጃዎች ጥራት በመተማመን እንዲሁም የቦርዱን ሥራ ከሚያደናቅፍና ዕምነት ጥያቄ ውስጥ ከሚከቱ ተግባራት ተቆጥበው በሕግ አግባብ ብቻ እንደሚንቀሳቀሱ በማመን፤ በማስጠንቀቂያ ዕግዱን ያነሣ መሆኑን ያሳውቃል።