የድምጽ መስጫ ቀን ቁሳቁሶች ወደመጋዘን እየገቡ ነው
ሰኔ 13 ቀን 2012 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ነሃሴ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ሊያከናውነው አቅዶ ለነበረው አገራዊ አጠቃላይ ምርጫ ለድምጽ መስጫ ቀን የሚያገለግሉ ቁሳቁሶች ግዥን ማጠናቀቁ ይታወሳል፡፡ በዚህም መሰረት ቀድመው ወደመጋዘን ከገቡት የመራጮች ምዝገባ ቁሳቁሶች በተጨማሪ የድምጽ መስጫ ቀን የሚያገለግሉ ቁሳቁሶች ወደመጋዘን እየገቡ ይገኛል፡፡ ለድምጽ መስጫ ቀን የተገዙ ቁሳቁሶች
1. ከግልጽ የሆነ ድምጽ መስጫ ሳጥን - 213,622
2. የሚስጥር ድምጽ መስጫ መከለያ - 156,600
3. የድምጽ መስጫ ቀን የአስፈጻሚዎች ቁሳቁስ- 58,400
4. ልዩ የምርጫ ቁሳቁሶች ማሸጊያ ፕላስቲክ ( plastic seal) እና የእሸጋ ስራ ስቲከሮች - 798,300
ሲሆኑ ከነዚህም መካከል በመጀመሪያ ዙር የራሳቸው ልዮ መለያ ቁጥር ያላቸው የድምጽ መስጫ ሳጥኖች ወደመጋዘን ገብተዋል፡፡ በቀጣይ ዙርም ቀሪዎቹ የድምጽ መስጫ ቀን ቁሳቁሶች መጋዘን ገብተው የሚጠናቀቁ ይሆናል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ