Skip to main content

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ክልል ካርታን መጋቢት 05 ቀን 2012 ዓ.ም. ይፋ አድርጓል

መጋቢት 5 ቀን 2012 ዓ.ም.

ይፋ የማድረጊያ ስነ ስርአቱን በንግግር የከፈቱት ብዙወርቅ ከተተ የቦርዱ አመራር አባል ሲሆኑ ጥሪ የተደረገላቸው የፓለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና የሚዲያ ተወካዮች ተገኝተዋል።

የህግ ባለሙያ ጌታቸው አሰፋ (ዶ/ር) የምርጫ ክልሎች አከላለል እና ህጋዊ ማእቀፍን አስመልክተው በህገ መንግሥቱ ስለተቀመጠው ምርጫ ክልል ምንነት፣ የምርጫ ክልሎችን መወሰኛ መስፈርትና ተያያዥ የህግ ማእቀፎችን አመላክተው ማብራሪያ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ለ2012 አጠቃላይ ምርጫ የምርጫ ክልሎች ካርታን በተመለከተ የተደረገው ዝግጅትን አስመልክቶ ሰፋ ያለ ገለጻ አድርገዋል፡፡ በገለፃቸውም ቦርዱ 547 የምርጫ ክልሎች መኖራቸውን ከመግለፅ ባለፈ በካርታ ይፋ የምርጫ ክልል ኖሮት እንደማያውቅ እና ይህ የመጀመሪያው የምርጫ ክልሎችን የሚያሳይ ካርታ እንደሆነ ተናግረዋል። ያሉትን የምርጫ ክልሎች በካርታ ከማሳየት ውጪ ቦርዱ አዲስ የምርጫ ክልል ዝግጅት እንዳላደረገም አሳውቀዋል።
በዚሁ የምክክር መድረክ ላይ ተሳታፊዎች ይፋ የተደረገውን የምርጫ ክልል ካርታዎችን የተመለከቱ ሲሆን ጥያቄዎንም አቅርበው በቦርዱ በኩል ማብራሪያዎች ተሰጥተዋል።

Share this post