ግንቦት 17,2011

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከሚያደርጋቸው ለውጦች መካከል የሚዲያ ተደራሽነትን መጨመር መረጃዎችን ለመገናኛ ብዙሃን ማቅረብ መሆኑ ይታወቃል፡፡ አዲስ ዘመን ጋዜጣ በግንቦት 16 ያወጣውን የሚከተለው ዘገባ መረጃ ለማግኘት ተቋማችንን መረጃ የጠየቀው ከቀናት በፊት ሲሆን በዜናው ላይ የተካተተው ዘገባ እጅግ የዘገየና ጊዜውን ጠብቆ ባለመውጣቱ ቦርዳችን መረጃን ከሰጠ ከቀናት በኋላ የወጣው ዜና በኋላ የተፈጠሩ ለውጦችን እንደማይገልጽ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡
በመሆኑም ቦርዱ መረጃ በሰጠበትና አዲስ ዘመን መረጃውን ባወጣበት የቀናት ክፍት ጊዜ የኢ-ዜማ ፓርቲ የእውቅና ጥያቄ ያስገባ ሲሆን ሰማያዊ እና መኢዴፓ የመክሰም ጥያቄ ለቦርዱ አቅርበዋል፡፡ 


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ