በአዲሱ የምርጫ እና የፓለቲካ ፓርቲዎች ረቂቅ ከምርጫ ጋር የተያያዙ አንኳር ለውጦች
ሐምሌ 12 2010
መረጃ -1
በተለያዩ አዋጆች ተካተው የሚገኙ ምርጫን ፖለቲካ ፓርቲዎችን እንዲሁም የምርጫ ስነምግባርን የሚመለከቱ ህጎች ጠንካራ ጎናቸውን እንዳለ በመጠበቅ በህግ ማእቀፎቹ ውስጥ የተገኙ ክፍተቶችን ከመዝጋት፣ ግልጽነታቸውን ከማሳደግ እና አፈጻጸማቸው የተሳለጠ እንዲሆን ከማስቻል አንጻር አስፈላጊ ማሻሻያዎች ተደርጎባቸው በአዲሱ ህግ ረቂቅ አዋጅ ውስጥ ተካትተዋል።