ኅዳር 17 2012

ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሲዳማ ህዝበ ውሳኔ አፈጻጸም ሂደት፣ በህዝበ ውሳኔ አስፈጻሚነት የሰራችሁ እና የአዲስ አበባ መስተዳድር ፕብሊክ ሰርቪስ ያወጣውን መስፈርት የምታሟሉ በምርጫ ማስፈጸም ስራችሁ ምክንያት ብቻ የጊዜ ገደብ ያለፈባችሁ አስፈጻሚዎች 

1. የአስፈጻሚነት ባጃችሁን
2. የ2010 ዓ.ም እና 2011 ዓ.ም ተመራቂነታችሁን የሚያሳይ የትምህርት ማስረጃችሁን
3. የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪነት መታወቂያ በመያዝ ህዳር 17 እና 18 ቀን 2012 ዓ.ም ሳሪስ በሚገኘው የቦርዱ ማሰልጠኛ ማእከል በመገኘት መመዝገብ እንደምትችሉ እናሳውቃለን፡፡ ቦርዱ በነዚህ ሁለት ቀናት የተመዘገቡ አስፈጻሚዎችን ስም ዝርዝር ለአዲስ አበባ ፕብሊክ ሰርቪስ ቢሮ የሚያስተላልፍ ሲሆን በነዚህ ቀናት ያልተመዘገቡ አስፈጻሚዎችን ስም ለመላክ እንደማይገደደድ ለማሳሰብ ይወዳል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
 

Announcment