ግንቦት 15,2011
ከምርጫ ቦርድ የተላለፈ ጥሪ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፊታችን ሰኞ ግንቦት 19 ቀን 2011 ዓ.ም “መገናኛ ብዙኃንና ምርጫ” በሚል ርእስ ከመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ጋር ምክክር አዘጋጅቷል፡፡ የምክክሩ አላማ መገናኛ ብዙሃንና ዲጂታል የመገናኛ መንገዶች በምርጫ ወቅቶች ስለሚኖራቸው ሚና እንዲሁም ከቦርዱ ጋር በአጋርነት የሚሰሩባቸው መንገዶች ላይ ለመወያየት ሲሆን፤ የሚዲያ ተቋማት በኢሜልና በደብዳቤ ጥሪ ተደርጎላቸዋል፡፡ ምክክሩ በሳፋየር አዲስ ሆቴል ከጠዋቱ 2፡30 የሚጀምር ሲሆን ጥሪ ለተደረገላቸው ብቻ ክፍት ነው፡፡
የምክክር መድረኩ ከተጠናቀቀ በኋላ ከቀኑ 8.30 ቦርዱ እያከናወናቸው ያሉ ስራዎችን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል፡፡ ጋዜጣዊ መግለጫው ለማንኛውም ሚዲያ ክፍት ሲሆን ጋዜጠኞች ከቀኑ 8፡30 ላይ ሳፋየር አዲስ ሆቴል በመገኘት መዘገብ ይችላሉ፡፡ ጥያቄ ወይም ማብራሪያ ለሚፈልጉ ፌስቡክ መልእክት ሳጥናችን ብታስቀምጡልን ወይም electionsethiopia [at] gmail.com ላይ ኢሜይል ብትጽፉልን አፋጣኝ ምላሽ እንሰጣለን፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቦርድ አባላት ጥቆማን ለመስጠት የሚከተለውን መረጃ መጠቀም ይችላሉ፡፡ በአዲሱ አዋጅ 1133/2011 መሰረት የአዳዲስ የቦርድ አባላት ምልመላ የሚመራው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ባቋቋሙት እጩ ቦርድ አባላት መልማይ ኮሚቴ ነው፡፡