የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተለያዩ ጊዜያት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የተለያዩ ውይይቶች በማድረግ ለቀጣዩ አገራዊ ምርጫ የሚያደርጋቸውን ዝግጅቶች ሲያሳውቅ እንደቆየ ይታወቃል፡፡ ቦርዱ በቅርቡ ካከናወናቸው ውይይቶች መካከል በጥቅምት ወር በአፍሪካ ህብረት በስብሰባ አዳራሽ ያከናወነው የምርጫ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ የሁለት ቀን አለም አቀፍ ጉባኤ እንዲሁም የምርጫ ጊዜያዊ የጊዜ ሰሌዳን አስመልክቶ ከሚመለከለታቸው አካላት ጋር ያደረገው ምክክር ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

በመሆኑም የነዚህ ውይይቶች ቀጣይ ክፍል የሆነውን የምርጫ ባለድርሻ አካላት ውይይት የካቲት 06 ቀን 2012 ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል አዘጋጅቷል፡፡ በዚህ የአንድ ቀን ውይይት ላይ ስለመጪው አገራዊ ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ፣   የምርጫ ዋና ዋና ተሳታፊዎች እና የትብብር ሃላፊነቶች እንዲሁም ስለቦርዱ ስራዎች ውይይት  የሚደረግ ሲሆን ዋና ዋና ባለድርሻ አካላትም ግብአት ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ እርስዎ/ድርጅትዎ ለቀጣዩ ምርጫ መሳካት ዋና ባለድርሻ እንደመሆንዎ መጠን በእለቱ ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በውይይቱ ላይ በመገኘት የድርሻዎን እንዲወጡ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡

Past