የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ህገ መንግሥት አንቀጽ 102 መሠረት የተቋቋመ ገለልተኛ እና ህገ መንግሥታዊ ተቋም ሲሆን ቦርዱ በአዋጅ ቁጥር 1133/2009 ምርጫን እና ህዝበ ውሳኔን በገለልተኝነት ለማስፈጸም በድጋሚ ተቋቁሟል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለደቡብ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ የስራ መደብ አመላካቾችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡ የክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊዋ/ው አጠቃላይ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱን ተግባራት የሚቆጣጠር/የምትቆጣጠር ይሆናል፡፡

ተፈላጊ የሰው ብዛት- 1

የባለሙያው ተጠሪነት - ለምክትል ሰብሳቢ ቢሮ

የስራ ቦታ - ሐዋሳ

የቅጥር ሁኔታ - በቋሚነት

ደሞዝ - በተቋሙ ስኬል መሰረት

በዚህም መሰረት በክልል የምርጫ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊነት በዕጩነት የሚቀርቡ አመልካቾች ማሟላት የሚኖርባቸው መስፈርቶች፡-

1. ኢትዮጵያዊ ዜጋ የሆነ/የሆነች፣

2. መደበኛ አድራሻው/ዋ በምርጫ ክልል ውስጥ ሆኖ የፌዴራሉን መንግስት እንዲሁም የሚወዳደርበትን ክልል የሥራ ቋንቋ (ማለትም አማርኛ) የመናገርና የመፃፍ ክህሎት ያለው/ያላት እንዲሁም ተጨማሪ በክልሉ የሚነገር ቋንቋን የሚችል/የምትችል ቢሆን/ብትሆን ይመረጣል፤

3. በአካባቢው ነዋሪ ሕዝብ አመኔታ ያተረፈ/ያተረፈች እና መልካም ሥነ ምግባር ያለው/ያላት፤

4. የማንኛውም ፖለቲካ ድርጅት አባል ያልሆነ/ያልሆነች፤

5. በትምህርት ዝግጅት በተለይ በሕግ፣ በፖለቲካ ሳይንስ፣ በህዝብ አስተዳደር፣ በስታቲስቲክስ፣ በማኔጅመንት፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂና ከምርጫ ጉዳዮች ጋር ተዛማጅነት ባላቸው የትምህርት ዘርፎች ቢያንስ በአንዱ የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው/ያላት፤

6. አመልካች የማስተርስ ዲግሪ ያላት/ያለው ከሆነ የአምስት ዓመት የሥራ ልምድ፤ የመጀመሪያ ዲግሪ ያላት/ያለው ከሆነ ደግሞ ሰባት ዓመት የሥራ ልምድ፤

7. የምርጫ ህጉን፣ ደንብና መመሪያዎችን አንብቦ/አንብባ በመረዳት ለሕዝቡ ማስረዳት የምትችል/የሚችል፤

8. የተቋም ነጻነትና እና በገለልተኛነት መርህ መሰረት ለማገልገል ዝግጁ እና ሙሉ ፍቃደኛ የሆነች/የሆነ።

ዋና ዋና ኃላፊነቶች

• የክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ የክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሰራተኞችን ይመራል፣ ይቆጣጠራል፣ ይደግፋል፡፡እንዲሁም በስሩ ያሉ ሰራተኞች ሀላፊነታቸውን በአግባቡ እየተወጡ መሆናቸውን እና አፈጻማቸውን በወቅቱ ይመዝናል፤

• የግዢ ሂደቶች በአግባቡ እና ጊዜያቸውን ጠብቀው እንዲሁም በመንግስት የፋይናንስ መመሪያ መሰረት መከናወናቸውን ለማረጋገጥ መደበኛ ክትትል ያደርጋል፤

• ቦርዱ በሚሰጠው አመራር መሰረት የአሰራር እና የፋይናንስ ችግሮችን የሚለዩ እና የሚፈቱ የመፍትሔ ሀሳቦችን ያዘጋጃል፣ ሂደቶችን ይመራል ፣ ይቆጣጠራል፤

• በክልሉ ውስጥ ስለምርጫ ክልሎች አመሰራረት ሀሳቦችን ያቀርባል፤

• በክልሉ ውስጥ የሚደረግ ምርጫን ያስተባብራል፤

• በክልሉ ውስጥ የምርጫ ሎጂስቲክስ በወቅቱ ወደምርጫ ክልሎች እና ምርጫ ጣቢያዎች መድረሳቸውን ይከታተላል፤

• በቦርዱ መመሪያ መሰረት በክልልና ምርጫ ክልል ደረጃ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምክር ቤትን ያደራጃል፤

• በክልሉ ውስጥ የሚካሄዱ የመራጮች ትምህርትን የሚሰጡ የሲቪክ ማህበራን ከቦርዱ የመራጮች ትምህርት የስራ ክፍል ጋር በመተባበር ይከታላል፣ ያስተባብራል፣እንዲሁም የመራጮች ትምህርት በህግ እና በስርአቱ መካሄዱን ያረጋግጣል፥

• ሌሎች በቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ እና የጽ/ቤት ሃላፊ የሚሰጡት ተግባራትን ያከናውናል።

አመልካቾች ለስራው ያላቸውን መነሳሳት የሚገልጽ አንድ ገጽ ማመልከቻ፣ የተሟላ ካሪኩለም ቪቴ፣ የትምህርት ማስረጃ እንዲሁም ሁለት ስለአመልካቹ ብቃት የሚገልጹ ለአመልካቹ ቅርብ ከሆኑ ሰዎች የተጻፉ የድጋፍ ደብዳቤዎችን በሚቀጥሉት 10 ቀናት ውስጥ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

የተሟላ ማመልከቻቸውን በኢሜል hr.dept [at] nebe.org.et እንዲሁም በፈጣን መልዕክት /EMS/ ወይም በፖስታ ሳጥን ቁጥር 40812 መላክ ይችላሉ፡፡

ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ!

Vacancy
March 20, 2022 -- Expired