በ2018 ዓ/ም ለሚካሄደው 7ኘው ዙር የጠቅላላ ምርጫ የህዝብ ተወካዮች እና የክልል ምክር ቤት አባላት ብዛት

PDFማጠቃለያ

ለ7ኛው ዙር የጠቅላላ ምርጫ የምርጫ ክልል ስም ዝርዝር እና የተወካዮች የወንበር ብዛት

PDFአዲስ አበባ ከተማ

PDFአፋር ክልል

PDFአማራ ክልል

PDFቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል

PDFድሬዳዋ ከተማ

PDFጋምቤላ ክልል

PDFሐረር ክልል

PDFኦሮሚያ ክልል

PDFሲዳማ ክልል

PDFሶማሊ ክልል

PDFደቡብ ኢትዮጵያ ክልል

PDFማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል

PDFደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ክልሎችን እና የምርጫ ጣቢያዎችን በመላው  ሀገሪቱ እንዲያቋቁም በአዋጅ ቁጥር 1133/2011 አንቀፅ 7 ሥልጣን ተሰጥቶታል፡፡ በዚህ መሠረት የተቋቋሙ የምርጫ ክልሎች በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 14 መሠረት ከታች የተዘረዘሩት ሥልጣን እና ተግባር ይኖራቸዋል። አንድ የምርጫ ክልል፦

  1. ቦርዱ በሚያወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት፦
    • የምርጫ ቁሳቁሶችን ለምርጫ ጣቢያዎች ያሰራጫል፣ 
    • ዕጩዎችን ይመዘግባል፣ መስፈርቱን ለሚያሟሉ ዕጩዎች የመታወቂያ ካርድ ይሰጣል፣ 
  2. ከምርጫ ጣቢያዎች የሚመጡ ሰነዶችና የምርጫ ቁሳቁሶች በአግባቡ ተሞልተው መምጣታቸውን  ያረጋግጣል፣ ይረከባል፣ በጥንቃቄ እንዲያዙ ያደርጋል፤ 
  3. ምርጫ ጣቢያዎች ተግባራቸውን በአግባቡ ማከናወናቸውን ይቆጣጠራል፤ 
  4. በህግ መሠረት ለሚቀርቡ ቅሬታዎችና አቤቱታዎች ውሳኔ ይሰጣል፤ 
  5. ከምርጫ ጣቢያ የመጡ የምርጫ ውጤቶችን በመደመር አሸናፊዎችን ከለየ በኋላ ጊዜያዊ ውጤት ለህዝብ ይፋ በማድረግ አስፈላጊ ቅጾችን በመሙላት ለቦርዱ ይልካል፤ 
  6. የዕጩ ወኪሎችን ዝርዝር ለምርጫ ጣቢያዎች ያስተላልፋል፤ 
  7. የምርጫ ክልሉን ሦስት አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አባላትን በዚህ አዋጅና ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት ያስመርጣል፤ 
  8. በምርጫ ክልሉ የሚወዳደሩ የፖለቲካ ድርጅቶችን የጋራ ምክክር ያስተባብራል፤ 
  9. የምርጫ ሂደትንና ውጤትን በተመለከተ ከምርጫ ጣቢያ ለሚመጡ አቤቱታዎች አፋጣኝ ምላሽ ወይም ውሳኔ ይሰጣል፤ 
  10. ቦርዱ  በሚያወጣው መመሪያ መሠረት የተመራጭነት መታወቂያ ለአሸናፊዎች ይሰጣል፤ 
  11. ከቦርዱ ወይም ከክልሉ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የሚሰጡትን  ሌሎች ተግባራት ያከናውናል።

በተመሳሳይ ሁኔታ በቦርዱ የሚቋቋም አንድ የምርጫ ጣቢያ በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 16 መሠረት ከታች የተዘረዘሩት ሥልጣን እና ተግባር ይኖሩታል፡-

  1. መራጮችን ይመዘግባል፤ 
  2. ከምርጫ ክልሉ የሚላኩ የምርጫ ቁሳቁሶችን ተቀብሎ በጥንቃቄ ይይዛል፤ 
  3. በህጉ መሠረት ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ ምርጫ ያካሂዳል፣ 
  4. በህጉ መሠረት የሚቀርቡለትን ቅሬታዎች ያስተናግዳል፣ 
  5. የተሰጠውን ድምፅ ቆጠራ በማካሄድ ጊዜያዊ የምርጫ ውጤት በማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በመለጠፍ ለህዝብ ያሳውቃል፣ 
  6. የምርጫ ሰነዶችና ቁሳቁሶች በአግባቡ ተሞልተው እና ተጠብቀው ለምርጫ ክልሉ እንዲላኩ ያደርጋል፣ 
  7. በዚህ አዋጅ አንቀጽ 15 (10) እና ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት የምርጫ ጣቢያውን አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ሁለት አባላት ያስመርጣል፣ 
  8. በምርጫ ሂደት ለሚከሰቱ ቅሬታዎችና አቤቱታዎች ፈጣን ምላሽ ይሰጣል፤ የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል፣ 
  9. ከቦርዱ፣ ከክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ ወይም ከምርጫ ክልል የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፡፡ 

ከዚህም በተጨማሪ  በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 17 መሠረት ቦርዱ ከምርጫ ክልላቸው ርቀው በካምፕ ለሚኖሩ ወታደሮች፣ ሲቪል ሠራተኞች እና ቤተሰቦቻቸው፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚማሩ ዜጎች፣ ከመኖሪያ ቀያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች እንዲሁም በእስር ቤት ለሚገኙ የመምረጥ መብታቸው ያልተገፈፈ ዜጎች በምርጫ የሚሳተፉበትን ሁኔታ ለማመቻቸት መራጮቹ በሚገኙበት ቦታ ወይም አካባቢ ልዩ ምርጫ ጣቢያ ሊያቋቁም ይችላል፡፡ 

ቦርዱ ስለ ምርጫ ክልሎች እና ስለ ምርጫ ጣቢያዎች ከታች የተረዘረዘሩትን የተለያዩ መመሪያዎች በማርቀቅ ላይ ይገኛል፡- 

  1. የክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት፣ የምርጫ ክልል እና የምርጫ ጣቢያ አደረጃጀት እና የምርጫ ዝግጅት መመሪያ 
  2. በልዩ ሁኔታ የሚቋቋሙ የምርጫ ጣቢያዎች መመሪያ እና 
  3. ተንቀሳቃሽ የምርጫ ጣቢያዎች እና የመራጮች ምዝገባ መመሪያ 

ስለ ምርጫ ክልሎች እና ምርጫ ጣቢያዎች ዝርዝር መረጃ ለማግኘት አዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 12 ጀምሮ እስከ አንቀጽ 17 ይመልከቱ፡፡