ጥቅምት 25  2012 

ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠ አስቸኳይ መግለጫ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሲዳማ ህዝበ ውሳኔን ለማከናወን ባለፉት ቀናት ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ከነዚህ ዝግጅቶች መካከል ስድስት ሺህ በላይ የምርጫ አስፈጻሚዎችን አሰልጥኖ በትላንትናው እለት ስምሪት የጀመረ ሲሆን የመራጮች ምዝገባ ቁሳቁስ ስርጭትም በዛሬው እለት ሲካሄድ ቆይቷል፡፡ ነገር ግን የተወሰኑ ርቀት ያላቸው የምርጫ ጣቢያዎች ቁሳቁስ አለመድረሱን ቦርዱ ስለተረዳ የመራጮች ምዝገባ መጀመሪያ ቀን በሁሉም ቦታዎች እኩል እንዲጀመር በማሰብ ጥቅምት 27 ቀን 2012 ዓ.ም እንዲሆን ዛሬ ጥቅምት 25 ቀን 2012 ዓ.ም ማምሻውን ባደረገው ስብሰባ ወስኗል፡፡

በመሆኑም የሚመለከታቸው አካላት እና ህብረተሰቡ የመራጮች ምዝገባ ጥቅምት 27 ቀን 2012 ዓ.ም እንደሚጀመር አውቀው ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ያሳውቃል፡፡

ጥቅምት 25 ቀን 2012 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ