የ6 ኛው ዙር ቀሪና የድጋሚ ምርጫ የሚካሄድባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ዝርዝር

PDFየምርጫ ጣቢያዎች ዝርዝር

ሀ) መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ለሚካሄደው ምርጫ ያሉ መረጃዎች

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ምርጫ የሚያካሂድባቸው ክልሎች ዝርዝር ከስር በሚገኝዉ ማስፈንጠሪያ ላይ ማግኘት ይቻላል

PDFየምርጫ ክልሎቸ ዝርዝር


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ለሚካሄደው ምርጫ ድምጽ የመስጠት ሂደት የሚከናወንባቸውን የምርጫ ክልሎች ዝርዝር ከስር በሚገኙት ማስፈንጠሪያዎች ላይ ማግኘት ይቻላል

PDFሐረሪ ክልል የምርጫ ጣቢያዎች

PDFሶማሌ ክልል የምርጫ ጣቢያዎች

PDFድሬዳዋ ከተማ ምርጫ ጣቢያዎች

PDFደ/ብ/ብ/ህ/ክ/ የምርጫ ጣቢያዎች

 


ለ) ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም. ለሚካሄደው ምርጫ ያሉ መረጃዎች

የምርጫ ክልል ቢሮዎች አድራሻ ከነልዩ የቦታ መጠሪያ ስማቸው

PDFየአዲስ አበባ ከተማ የምርጫ ክልሎች አድራሻ

PDFየሐረሪ ክልል የምርጫ ክልሎች አድራሻ

PDFየቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የምርጫ ክልሎች አድራሻ

PDFየኦሮሚያ ክልል የምርጫ ክልሎች አድራሻ 

PDFየድሬዳዋ ከተማ የምርጫ ክልሎች አድራሻ

PDFየሶማሌ ክልል የምርጫ ክልሎች አድራሻ

PDFየሲዳማ ክልል የምርጫ ክልሎች አድራሻ

PDFየአማራ ክልል የምርጫ ክልሎች አድራሻ

PDFየአፋር ክልል የምርጫ ክልሎች አድራሻ

PDFየደ/ብ/ብ/ህ ክልል የምርጫ ክልሎች አድራሻ

PDFየጋምቤላ ክልል የምርጫ ክልሎች አድራሻ

የምርጫ ክልሎች ዝርዝር  

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አጠቃላይ ምርጫ የሚከናወንባቸው የምርጫ ክልሎች ከስር በሚገኙት ማስፈንጠሪያዎች ላይ ማግኘት የሚቻል ሲሆን እያንዳንዱ ክልል ውስጥ ለፌዴራል (የተወካዮች ምክር ቤት) መቀመጫ እና ለክልል ምክር ቤት መቀመጫ የሚመረጥባቸው የምርጫ ክልሎች እና የመቀመጫዎች ብዛት ዝርዝር ማግኘት ይቻላል። በአጠቃላይ አሁን የጊዜ ሰሌዳ በወጣለት 6ተኛው አገር አቀፍ ምርጫ 673 የምርጫ ክልሎች ላይ ምርጫ ይደረጋል።  

PDFአዲስ አበባ ከተማ

PDFአፋር ክልል 

PDFአማራ ክልል

PDFቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል

PDFድሬዳዋ ከተማ

PDFጋምቤላ ክልል

PDFሐረር ክልል

PDFኦሮሚያ ክልል

PDFሲዳማ ክልል

PDFደቡብ ብሔሮች ብሔረሠቦች እና ህዝቦች ክልል

PDFሶማሊ ክልል

የምርጫ ጣቢያዎች ዝርዝር

ለ6ተኛው ጠቅላላ ምርጫ በክልሎች እና በአገር አቀፍ ደረጃ አገልግሎት ላይ የሚውሉ ምርጫ ጣቢያዎች ዝርዝር የሚከተለው ሲሆን የእያንዳንዱ ክልል የምርጫ ጣቢያ ዝርዝር ከስር ባሉት ሊንኮች ላይ ይገኛል።

PDFየምርጫ ጣቢያ ዓይነት አጠቃላያ መግለጫ - 49,407

PDFአዲስ አበባ ከተማ - 1,848

PDFአፋር ክልል - 1,432

PDFአማራ ክልል -12,199

PDFቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል - 699

PDFድሬዳዋ ከተማ -305

PDFጋምቤላ ክልል - 431

PDFሐረር ክልል - 285

PDFኦሮሚያ ክልል - 17,623

PDFሲዳማ ክልል - 2,247

PDFደቡብ ብሔሮች ብሔረሠቦች እና ህዝቦች ክልል - 8,281

PDFሶማሊ ክልል - 4,057

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ክልሎችን እና የምርጫ ጣቢያዎችን በመላው  ሀገሪቱ እንዲያቋቁም በአዋጅ ቁጥር 1133/2011 አንቀፅ 7 ሥልጣን ተሰጥቶታል፡፡ በዚህ መሠረት የተቋቋሙ የምርጫ ክልሎች በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 14 መሠረት ከታች የተዘረዘሩት ሥልጣን እና ተግባር ይኖራቸዋል። አንድ የምርጫ ክልል፦

  1. ቦርዱ በሚያወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት፦
    • የምርጫ ቁሳቁሶችን ለምርጫ ጣቢያዎች ያሰራጫል፣ 
    • ዕጩዎችን ይመዘግባል፣ መስፈርቱን ለሚያሟሉ ዕጩዎች የመታወቂያ ካርድ ይሰጣል፣ 
  2. ከምርጫ ጣቢያዎች የሚመጡ ሰነዶችና የምርጫ ቁሳቁሶች በአግባቡ ተሞልተው መምጣታቸውን  ያረጋግጣል፣ ይረከባል፣ በጥንቃቄ እንዲያዙ ያደርጋል፤ 
  3. ምርጫ ጣቢያዎች ተግባራቸውን በአግባቡ ማከናወናቸውን ይቆጣጠራል፤ 
  4. በህግ መሠረት ለሚቀርቡ ቅሬታዎችና አቤቱታዎች ውሳኔ ይሰጣል፤ 
  5. ከምርጫ ጣቢያ የመጡ የምርጫ ውጤቶችን በመደመር አሸናፊዎችን ከለየ በኋላ ጊዜያዊ ውጤት ለህዝብ ይፋ በማድረግ አስፈላጊ ቅጾችን በመሙላት ለቦርዱ ይልካል፤ 
  6. የዕጩ ወኪሎችን ዝርዝር ለምርጫ ጣቢያዎች ያስተላልፋል፤ 
  7. የምርጫ ክልሉን ሦስት አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ አባላትን በዚህ አዋጅና ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት ያስመርጣል፤ 
  8. በምርጫ ክልሉ የሚወዳደሩ የፖለቲካ ድርጅቶችን የጋራ ምክክር ያስተባብራል፤ 
  9. የምርጫ ሂደትንና ውጤትን በተመለከተ ከምርጫ ጣቢያ ለሚመጡ አቤቱታዎች አፋጣኝ ምላሽ ወይም ውሳኔ ይሰጣል፤ 
  10. ቦርዱ  በሚያወጣው መመሪያ መሠረት የተመራጭነት መታወቂያ ለአሸናፊዎች ይሰጣል፤ 
  11. ከቦርዱ ወይም ከክልሉ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የሚሰጡትን  ሌሎች ተግባራት ያከናውናል።

በተመሳሳይ ሁኔታ በቦርዱ የሚቋቋም አንድ የምርጫ ጣቢያ በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 16 መሠረት ከታች የተዘረዘሩት ሥልጣን እና ተግባር ይኖሩታል፡-

  1. መራጮችን ይመዘግባል፤ 
  2. ከምርጫ ክልሉ የሚላኩ የምርጫ ቁሳቁሶችን ተቀብሎ በጥንቃቄ ይይዛል፤ 
  3. በህጉ መሠረት ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ ምርጫ ያካሂዳል፣ 
  4. በህጉ መሠረት የሚቀርቡለትን ቅሬታዎች ያስተናግዳል፣ 
  5. የተሰጠውን ድምፅ ቆጠራ በማካሄድ ጊዜያዊ የምርጫ ውጤት በማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በመለጠፍ ለህዝብ ያሳውቃል፣ 
  6. የምርጫ ሰነዶችና ቁሳቁሶች በአግባቡ ተሞልተው እና ተጠብቀው ለምርጫ ክልሉ እንዲላኩ ያደርጋል፣ 
  7. በዚህ አዋጅ አንቀጽ 15 (10) እና ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት የምርጫ ጣቢያውን አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ሁለት አባላት ያስመርጣል፣ 
  8. በምርጫ ሂደት ለሚከሰቱ ቅሬታዎችና አቤቱታዎች ፈጣን ምላሽ ይሰጣል፤ የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል፣ 
  9. ከቦርዱ፣ ከክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ ወይም ከምርጫ ክልል የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፡፡ 

ከዚህም በተጨማሪ  በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 17 መሠረት ቦርዱ ከምርጫ ክልላቸው ርቀው በካምፕ ለሚኖሩ ወታደሮች፣ ሲቪል ሠራተኞች እና ቤተሰቦቻቸው፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚማሩ ዜጎች፣ ከመኖሪያ ቀያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች እንዲሁም በእስር ቤት ለሚገኙ የመምረጥ መብታቸው ያልተገፈፈ ዜጎች በምርጫ የሚሳተፉበትን ሁኔታ ለማመቻቸት መራጮቹ በሚገኙበት ቦታ ወይም አካባቢ ልዩ ምርጫ ጣቢያ ሊያቋቁም ይችላል፡፡ 

ቦርዱ ስለ ምርጫ ክልሎች እና ስለ ምርጫ ጣቢያዎች ከታች የተረዘረዘሩትን የተለያዩ መመሪያዎች በማርቀቅ ላይ ይገኛል፡- 

  1. የክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት፣ የምርጫ ክልል እና የምርጫ ጣቢያ አደረጃጀት እና የምርጫ ዝግጅት መመሪያ 
  2. በልዩ ሁኔታ የሚቋቋሙ የምርጫ ጣቢያዎች መመሪያ እና 
  3. ተንቀሳቃሽ የምርጫ ጣቢያዎች እና የመራጮች ምዝገባ መመሪያ 

ስለ ምርጫ ክልሎች እና ምርጫ ጣቢያዎች ዝርዝር መረጃ ለማግኘት አዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 12 ጀምሮ እስከ አንቀጽ 17 ይመልከቱ፡፡